Breaking News
Home / Amharic / መንግስታዊነት ሆይ ወዴት አለሽ? christian tadele – member of parliament

መንግስታዊነት ሆይ ወዴት አለሽ? christian tadele – member of parliament

መንግስታዊነት ሆይ ወዴት አለሽ?
*****
 
 
ሕወኃት አሸባሪ ድርጅት ተብሎ የተፈረጀው በሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ነው። የሰላም ስምምነት ፊርማ እንደተጠበቀ ሆኖ በሕግ ሕወኃት አሁንም ድረስ አሸባሪነቱ ያልተሰረዘለት ቡድን ነው። አስፈፃሚው አካል በማናለብኝነት የሚሰራውን ሕጎችን የመጣስ በጎ ያልሆነ ልምምድ የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት የመቆጣጠር ሕዝባዊ ኃላፊነት አለበት። ለስነስርዓታዊ ጉዳዮችም ከሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት በላይ ማን ሊጨነቅ ይችላል?
እነዚህ መንግስታዊ ባሕሪያት ሁሉ ግን በብልጽግና መሩ የኢትዮጵያ መንግስት ዘንድ ከመጤፍ የሚቆጠሩ ሆነዋል። የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት አፈጉባዔ የተከበሩ ታገሰ ጫፎ የመቀሌ ጉብኝት የመንግስትነት ወግ ብልሽት ዓይነተኛ ምሳሌ ሆኖ ለትውልድ አብነት ሊጠቀስ የሚችል ነው። መንግስታዊነት ሆይ ወዴት አለሽ? ከዚህ በኋላስ በምክርቤት ጉባዔዎች የስነስርዓት ጥያቄዎችን የማስከበር ሞራላዊ ቅቡልነት ይኖር ይሆን?
(ይኼ የስነስርዓት ጥያቄዬ የሰላም ስምምነቱን ከመቀበል እና አለመቀበል ጋር ግንኙነት የለውም።)
 

Check Also

ድሮን ሲያስተኩስ የነበረው ባንዳ በፋኖ ተያዘ ! እኔን ያየህ ተቀጣ !

ከጎጃም አማራ ፋኖ የተሰጠ መግለጫ – ዘመነ ካሴ – Amhara FANO Gojjam

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.