Breaking News
Home / Amharic / መብራቱ ገብረህይወት ማነው ?

መብራቱ ገብረህይወት ማነው ?

ከማነው እውነተኛ 

 

በረከት ስምዖን (መብራቱ ገብረህይወት ማነው) ማን ነው?
ለማንስ አገለገለ ማንንስ ጨቆነ?
አቶ በረከት ስምዖን ሠሞኑን በስርቆት እና እምነት በማጉደል የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ወደ ከርቸሌ መውረዳቸውን ተከትሎ በሁለት የተከፈሉ ሀሳቦች ይጎርፋሉ፡፡
ሀሳቦቹም
1. አንደኛው በረከት ህይወቱን በሙሉ ለህዝብ በለፋ ይህ አይገባውም የሚል ሲሆን ( ከወደ ትግራይ የሚተሙ ሀሳቦች ናቸው)
2. በረከት ስምዖን የአንድ ክልል ዘር ያጠፋ ያሠረ የጨፈጨፈ ጨካኝ አረመኔ ወደ እስር ቤት መውረዱ ትክለኛ ስለሆነ ደስተኛ እና ህግ መኖሩን ያመላከተ መሆኑን በየ አቅጣጫው የሚተሙ ሀሳቦች አሉ፡፡
*** የተለያዩ ሀሳቦች መምጣታቸው ምክንያቱ ምንድን ነው?
በመጀመሪያ የሀሳቦቹ የሚዛን ችግር እና በጥቅም የተመሠረተ ካልሆነ በስተቀር ሀሳቦቹ በእያንዳንዱ ጫማ ከቆምን ልክ ናቸው፡፡
የመጀመሪያውን ስንመለከት በረከት በ44 አመት የአስተሳሰብ ስራ እና በ27 አመት የኦፕሬሽን ተግባሩ አማራን እየጎዳ እየጠላ ታሪኩን እያዛባ ይዞታውን እየነጠቀ የህዝቡን ጥቅም እያሳጣ ግን ደግሞ ወክልናውን እሱና መሠሎቹ ተቆናጠውበት ኑረዋል፡፡ከዚህ በተቃራኒ ደግሞ አማራው ጥቅሙ ተነጥቆ ጥቅም የሚሠጡ በጎ ታሪክ የሚፃፍላቸው እና ይዞታ የሚደረብላቸው የክልል አንድ ሠወች አሉ፡፡
ታዲያ ዛሬ የበረከት እጣ ፈንታ እስር ቤት መሆን የለበትም ቢሉ አይገርም ምክንያቱም ፖለቲካ በኢኮኖሚ መሻሻል እንጅ እኩል እንራመድ የሚል እውነታ የለውምና፡፡እነዛ ሠወች ደግሞ በበረከት አቅም በተከናወኑ ልማቶች ተጠቃሚ ሆነዋል እና፡፡
ወደ ሁለተኛው ሀሳብ ስመጣ በረከት መታሠሩ ህግ መኖሩን የሚያሳይ የዘራውን እንዳጨደ እና ደስታም ጭምር የተናነቀው አስተያየት ይተማል፡፡ይህም ማንም የሚያውቀው ሀቅ ነው፡፡
በረከት ማነው ካልን በረከት
አማራ እየመሠለ አማራን የገደለ አማራን ያሠረ አማራን ያንኮላሸ አማራን ድሃ ያደረገ፡ጠላተ አማራ(ፀረ- አማራ) ነው፡፡ይህን ስል ያለመገለጫ አይደለም፡፡
_ በረከት እነ ክንፈ ዳኘው እየዘረፉ ምንም ያልነኩትን እና የሌባ ነቀርሳ የሆነው መላኩ ፈንታን ያሳሰረ ጎንደሬ ነኝ እያለ የጎንደር ጠላት ነው፡፡መላኩ ፈንታ አምስት አመት በበረከት ትዛዝ ታጉሮ መረጃ ጠፍቶ ሳይወሠንበት የተፈታ የኖረ ምሁር ነው፡፡መላኩ ፈንታን ለስር የዳረገው የበረከት ሚስት በህወጥ መንገድ ያስገባችውን ዘመናዊ ካሜራ እንደማንኛውም ተቀርጦ መግባት አለበት በማለቱ በህወሃት ጀነራል የታሠረ ንፁህ አማራ ነው፡
_ በረከት በመድረክ የተናገሩ እና የአማራ ተቆርቋሪ የሆኑ አመራሮችን እያሳደደ ተምክህተኛ በሚባል የሴራ ቃል ተጠቅሞ እያባረረ አማራን ተቆርቋሪ ያሳጣ እና የሡን ቃል የተቀበልን ብቻ ይዞ የቀጠለ አቅመ ቢስ መዋቅር ፈጥሮ አማራን ከጥቅም የጎተተ ጠላተ አማራ ነው፡፡
_ በረከት እንደነ ጌተቸው አሠፋ ያሉ አምባገነኖችን ፈልፍሎ የአማራን እና የኦሮሞን ምሁር ወጠት እና ሠራዊት እንዲሠቃዩ ያደረገ የአንድነት እና የፍቅር ፀር ነው
_ በረከት ለአማራ የሚያቀነቅን ምሁርም ይሁን ተቆርቋሪ ዜጋ የማይወድ የአማራ አንድነት የሚያሠጋው ፀረ አማራ ነው፡፡በረከት ከመለስ ጋር ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ Award ያገኘውን የኢትዮጵያውን የህክምና ፈላስፋ ፕ/ር አስራት ወ/የስን አማራ በመሆኑ የብቃት ችግር አለበት ብለው ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ያስወገዱ ቆይተውም ወደ እስር ወርውረው ለሞት ያበቁ በተለይም በረከት አማራን ወከልኩ እያለ የአማራ ጠላት ነው፡፡
_ በረከት እንዳያድ ጠፍሮ የያዘውን ጥረትን እያከሠረ ለEFFORT ሲያዘረፍ የኖረ ለአማራ ልማት እንቅፋት ነው፡፡የሚገርመው የአማራን እና የኢትዮጵያን አንጡራ ሀብቶች እየጎረጎጎረ ለህወሃት ያቀበሌ ሠይጣን ነው፡፡የጎንደር ግዙፍ ጀነሬተር የተወሠደው በበረከት አማከኝነት ነው፡፡እነ ሡር ኮንስትራክሽን ወደ EFFORT የሔዱት በሡ አስተባባሪነት ነው፡፡ሡር ኮንስትራክሽን የኢትዮጵያ፡የመንገድ ስራ ድርጅት የነበረ ነው፡፡
_ በረከት አማራን ለማፋጀት ቅማንት እና አማራ ብሎ ከፋፍሎ ዛሬ የሚያፋጀን ሴረኛ ሠው ነው፡፡
እነዚህን በሰነድ የተቀመጡ ገሀድ ይሁኑ እንጅ በረከት በአማራ ህዝብ ላይ ያላደረገው ነገር የለም፡፡በዚህም ይህ ህዝብ በበረከት መታሠር ባይደሠት ነበር የሚገርመው እንጅ መደሠቱ ልክ ነው፡፡

Check Also

Ethnic Terrorism Continues to Stalk Ethiopia.

JANUARY 20, 2023 BY GRAHAM PEEBLES FacebookTwitterRedditEmail   Where there is division there will be conflict. …

የዘውድ ስርአት ሁሉንም ኢትዮጵያውያን ማስተባበር ይችላል! (ግዛቸው ጥሩነህ (ዶ/ር))

የዘውድ ስርአት ሁሉንም ኢትዮጵያውያን ማስተባበር ይችላል!   ግዛቸው ጥሩነህ (ዶ/ር) ከአንድ አመት በላይ በኢትዮጵያ ውስጥ በተካሄደው የእርስበርስ ጦርነት፤ በብዙ መቶ ሺ የሚቆጠሩ …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.