Breaking News
Home / Amharic / መልእክቴን ለዝናሽ ታያቸው አድርሱልኝ። share

መልእክቴን ለዝናሽ ታያቸው አድርሱልኝ። share

“ሳይቃጠል በቅጠል !!” ማለት ይሄኔ ነው !! ስለዚህች ሴት መናገር አልፈልግም ነበር። እስከዛሬም ስሟን አንስቼ አላውቅም። እውነት ለመናገር አክብሮትም፣ አዘኔታም ስለነበረኝም ጭምር፣ እሷም ያው ከራሷም ሆነ ከሌላ በመጣ ግፊት የምታደርገው እንቅስቃሴ ለጥቂት ሰዎችም ቢሆን ቢጠቅም እንጂ ጉዳት ያስከትላል ብዬ ስላላሰብኩ ምንም አለማለትን ነበር የምመርጠው። ዛሬ ግን ይህን ለማለት ያነሳሳኝ ለክፉ ሥርዓት መጠቀሚያ ለመሆን ዳዴ እያለች መሆኑን ከዛሬው የዳቦ ቤት ምረቃ ንግግሯ ላይ ከፍተኛ እና የህዝብን ሰቆቃ የመካድ ፋውል ስትሰራ ስላየሁኝ የሱ ይበቃናል አንቺ ተጨምረሽ በቁስላችን እንጨት አትስደጂ ለማለት ነው።

የወያኔ እና የኦነግ አንባገነን መሪዎች ከሌሎች ምሁራኖች እና የተለያየ ሙያ ካላቸው አገራቸውን በቅንነት ለማገልገል ከሚፈልጉ ዜጎች ጋር ለመስራት የማያስቸል የማን አለብኝነት ቁመና ላይ ሲደርሱ ዙሪያ ገባውን እንዲያደናዝዙላቸው እና የስርቆት ሚስጥራቸውን ጠብቀው በዝርፊያ ስራቸው እንዲያግዟቸው ሲፈልጉ ለሚስቶቻቸው ገንዘብ እና ጥቂት ስልጣን ይሰጧቸው እና ህዝብ ላይ እንዲቀብጡ ፈተው ይለቋቸዋል። ሴቶቹ ደግሞ ፍራቻ ይሁን፣ አጋጣሚውን ተጠቅመው ገንዘብና ዝና ለማትረፍ የውስጣቸውን የሚያውቁት እነሱ ናቸው ግን ካለ ስሪታቸው የሚይዙ የሚጨብጡትን ያጣሉ። ያለ ስሪታቸው ያልኩት በምክኒያት ነው::

አዜብ መስፍን እንደዚያ ተብለጥልጣ መታየት የጀመረችው ኢህአዲግ የምርጫ ዘጠና ሰባቱን ምርጫ በድል ለመወጣት በግምት ሁለት አመት ሲቀረው በየክልሉ የምትሄድበትን አካባቢ የባህል ልብስ እየለበሰች (በወቅቱ ሱርማ ስትሄድ ከንፈሯን ትቀደድ እንደሆነ እናያታለን እየተባለ ሙድ ይያዝባት ነበር) መዞር ከጀመረች እና የምርጫው ውጤት ከወንበራቸው ለግዜው ባይፈነቅላቸውም እንደበፊቱ ችላ በማለት በስልጣን መቆየት እንደማይቻል ሲባንኑ ባሏ የማሰር፣ የመግደል፣ በአጠቃላይ አንድ አንባገነን መሪ ሊሆነው የሚችለውን ሁሉ ሲሆን እርሷ ደግሞ የግል ኢኮኖሚያቸውን ለማጠናከር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከባለሃብቶች ጋር በመጣመር አገር የማራቆት ስራ ላይ ከተሰማራች በኋላ ነው።

ስለዚህ እስከ 1995 ዓ. ም. ድረስ የተለየ ግብዣ ላይ፣ አንዳንድ ስብሰባዎች ላይ፣ አብረው የውጪ ጉዞ ሲኖራቸው ሲወጡና ሲገቡ አውሮፕላን ማረፊያ ዜና ላይ ብትታይ ነው እንጂ ብዙም አናውቃትም። እንዲያውም በወቅቱ መለስ ዜናዊ ስለ አለመታየቷ ተጠይቆ ብዙም መታየት እንደማትፈልግ እና ሚዲያ እንደማትወድ ተናግሮ እንደነበር አስታውሳለሁ።

ዝናሽ ታያቸውም ምንም እንኳን ከመጀመሪያው ጀምራ ከስክሪን ባትርቅም ከዚያ በፊት የሰከነ እና ልጆቿን ማሳደግ ላይ ትኩረት ያደረገ ኑሮ ትኖር እንደነበረ በወፍ በረር ሰምተናል:: አሁን ግን አባትየው መለስ የሄደበትን አካሄድ ልጅየው ናፒም ተከትሎ የእናትየውን የአዜብን ቦታ እንድትተካ ዝኑን ፈቶ ለቆብናል። ይኸው ነገርየው ማለቴ የገንዘቡ ምንጭ “የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው” ቢሆንም ዳቦ ቤቷን ከፍታ ለካሜራ ግብዓት ከመሆን አልፋ “ዳቦ ፋብሪካ ተከፍቶላችሁ ብሉ እየተባላችሁ ነው።” ሰላማችሁንም እናንተው ናችሁ እያደፈረሳችሁ ያላችሁት አይነት እንድምታ ያለው ደግ የሚመስል ክፉ ንግግር መናገር ጀመረች። ከላይ እንዳነሳሁት አዜብ መስፍንም እንዲሁ ነበር የሚያደርጋት::

ህዝቧ የአስቴርን ሚና ተጫውታ የሞትን አዋጅ ታሽርልናለች ብሎ ሲጠብቅ ዳቦ እየበላህ ሙት ብላው አረፈች። እሷ ይህንን ስትናገር አማራው በሚሊዮኖች ሞቷል የተረፈውም እንዲሁ በሚሊየኖች ተፈናቅሎ ቁር እና ሃሩር እየተፈራረቁበት የሚልስ የሚቀምሰው አጥቶ ሜዳ ፈሷል። እሷ ይህንን ስታወራ አዲስ አበባ ዙሪያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቤታቸው በዶዘር ተንዶባቸው በሚያሰቅቅ ሁኔታ ያለ መጠለያ ቀርተዋል። እሷ ይህንን ስትደሰኩር እና ህዝብ በገዛ እጁ ሰላሙን እንዳጣ ልታሳምነው ስትሞክር በወለጋ በየቀኑ ሰው እየተጨፈጨፈ ያድራል። በቦረና ረሃብ ገብቶ ስውና ከብቱ እንደ ቅጠል ይረግፋል:: በጉራጌ ውሃ የጠማው ጥይት ይጠጣል፣ በባሏ እና ግብረ አበሮቹ እኩይ ተግባር አገር አስተሳሳሪዋ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ታምሳለች። የኑሮ ውድነቱ የማይቀመስ ሆኖ ብዙዎቹን ከመኖር ጨዋታ ውጪ እያወጣቸው ነው:: ምኑ ቅጡ! የሰው ልጅ በሃያ እንደኛው ክ/ዘመን ይደርስበታል ተብሎ በማይታሰብ ሁኔታ እየተንገላታ ባለበት ሁኔታ ጥቂት የእናትነት ርህራሄ በማሳየት ፋንታ የተጨማለቀ ፖለቲካ ውስጥ ገብታ መዳከር ያለባት አይመስለኝም:: ብዙ ሳትነካካ ትሰክን ዘንድም ምክሬ ነው:: የህዝቡን ቁስል ለመጓጎጥ ውድ ባለቤቷ ይበቃናል።

አይዳ (ቃል እና ቀለም)

Check Also

በአሜሪካን ሀገር የምትኖሩ የአማራ ማህበራትና የአማራ ልጆች የት ነው ያላችሁት?? Share!

ድሮን ሲያስተኩስ የነበረው ባንዳ በፋኖ ተያዘ ! እኔን ያየህ ተቀጣ !

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.