Breaking News
Home / Amharic / ለአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተሰጠ የመልስ ምት !

ለአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተሰጠ የመልስ ምት !

ለብአዴን ቁንጮው ለአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተሰጠ የመልስ ምት አቶ ገዱ በንግግራቸው አማራ የተወረረው ስላልተደራጀ ነው ብለው አፍ ሞልቶ ሲናገሩ ትንሽም አላፈሩም ፋኖን እያሳደዱ ሲያስገድሉና እንዳይደራጅ ሲያደርጉ የኖሩት ሰውዬ ዛሬ ደርሰው ህዝቡን ተጠያቂ ማድረግ ትልቅ ነውርነው እጅግም ያሳፍራል
ከዚህ በታች የመልስ ምት የሰጣቸው ዴቭ ዳዊት ነው።
 
ይድረስ ለገዱ አንዳርጋቸው እና ቀሪ ብአዴናዊያን =======
እናንተ በህዝባችን ጫንቃ ላይ ተቀምጣችሁ፥ ወጣቱ በራሱ መንገድ እንዳይደራጅ ስትከለክሉትና ስታሳድዱት ነበር፤ በራሳችሁ መንገድም ልታደራጁት ፈቃደኛ አልነበራችሁም። ይህንን የአደባባይ ምስጢር ጠንቅቆ የተረዳው ጠላት ደግሞ፥ የራሱን ምልምል ነጭ-ለባሽ ባንዳዎች እናንተ በምታስተዳድሩት ክልል መልምሎ ቢያደራጅና ለእኩይ አላማው ቢጠቀምባቸው፥ ዛሬ እንዴት ሊገርማችሁ ቻለ⁉ ለዚህ ሁሉ በዋናነት ተጠያቂው ከእናንተ ውጪ ማን ሊሆን ይችላል⁉ የአማራን ህዝብ ሰብሳቢ የሌለው orphan ማድረጋችሁ ሳያንስ፥ በራሱ መንገድ እንኳ እንዳይሰባሰብ በጫትና በሀሽሽ የደነዘዙ ካድሬዎች አሰማርታችሁ ስትከፋፍሉት፣ ስታዋክቡት፣ ተስፋ ቆርጦ እንዲሰደድ ስታደርጉት ነበር፤ ያም አልበቃ ሲል የሀገሪቱን ጦር አሰማርታችሁ በጭንቅ የገዛትን መሣሪያ ስትገፍፉት ነው የኖረው። Invest ባላደረጋችሁበት ህዝብ ላይ፥ fat dividend ለመውሰድ አኮፋዳችሁን ይዛችሁ ብትመጡ፥ ውጤቱን ይኸው እንዳያችሁት ነው፦ Garbage in Garbage out‼‼ ጠላትማ የራሱን ህዝብ ከማደራጀት አልፎ፥ በእናንተ ጓዳ ውስጥ ነጭ-ለባሽ ባንዳ መልምሎ ማደራጀቱ የሚመሰክረው አንድ መራራ እውነት ቢኖር፥ የትናንት አሳዳሪ-ጌቶቻችሁ፥ እናንተ ባሪያዎቻቸው አቅመ-ቢስና ተላላኪ ከመሆን በዘለለ በራሳችሁ ምንም መስራትም ይሁን ህዝብን አደራጅቶ የማብቃት ችሎታ እንደሌላችሁ ማወቃቸውና፥ ያንንም ክፍተት እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ ብቻ ነው‼
ከተላላካችሁበት የሰላሳ ዓመት የባርነት ዘመናችሁ፥ አንዷን አመት ህዝብን ለማንቃትና ለማደራጀት አውላችሁት ቢሆን ኖሮ፥ አሁን የታየው ውድቀትና ውርደት ባልተከሰተ ነበር‼‼
ራዕይ አልባ፣ በዝርዉ የተበተነ ትውልድና ህዝብ ስትፈጥሩ ጥቂት ያልሰቀጠጣችሁ፥ ዛሬ ደርሶ ተግሳፅ አውራጅ፣ መካሪና ወቃሽ መስሎ መቅረብ ማንንም አይረዳም፤ እናንተንም የጠቆረ የተላላኪነት ታሪካችሁን ይበልጥ ያጠቁረው ካልሆነ በቀር‼‼‼
የታሪክና የትውልድ ተወቃሾቹ ፥ በህዝባችን ጫንቃ ላይ ተቀምጣችሁ እንዳይነቃ፣ እንዳይሰለጥን፣ እንዳይደራጅ በተለያየ መንገድ ስታመክኑት የኖራችሁ እናንተዉ ራሳችሁ ናችሁ‼‼‼
ዴቭ ዳዊት።

Check Also

ለኢትዮ 360 ተመልከቾችና ደጋፊዎች በሙሉ የቀረበ ጥሪ !!

ለኢትዮ 360 ተመልከቾችና ደጋፊዎች በሙሉ የቀረበ ጥሪ !! ********************************************** #ሼር እናድርግ #እናዛምት ከቅዳሜ ግንቦት 5/2015 …

ቤተክርስቲያኒቱ ከባለፈው የበለጠ ብርቱ ፈተና እየመጣባት ነው። መሳይ መኮነን

ቤተክርስቲያኒቱ ከባለፈው የበለጠ ብርቱ ፈተና እየመጣባት ነው። እነአብይ አሁን ብቻቸውን አይደሉም። ከእነጌታቸው ረዳ ጋር ተጣምረው …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.